የደቡብ አፍሪካ የህግ አስከባሪዎች ባለፉት ጥቂት ወራቶች ብቻ ከ1ነጥብ 2ቢሊየን በላይ ግምት ያለው ኮኬይን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ፡፡

የህግ አስከባሪዎቹ ይህንን ያህል መጠን ያለው ኮኬይን በቁጥጥር ስር ያዋሉት በሀገሪቱ በሶስት ዋና ዋና ከተሞች ነው ተብሏል፡፡የሀገሪቱ የህግ አስከባሪዎች ከባህር እና ከወንጀል መከላከል ከፍተኛ መርማሪዎች ጋር በጋራ ባከናወኑት ጥብቅ ክትትል ነው ኮኬይኑ ሊያዝ የቻለውም ተብሏል፡፡

የደርባን ፖሊስ አዛዥ ኮረኔል ፊላኒ ኑኳላሲ እንደተናገሩት ኮኬይኑ የእንስሳት መኖ በጫኑ ኮንቴነሮች ስር ተጭኖ ወደ ከተማ ሊገባ ሲል በህብረተሰቡ እና በፖሊስ ጥምረት ሊያዝ ችሏል ብለዋል፡፡

26 አይነት የንግድ ምልክት የተደረገባቸው የኮኬይን ምርቶች በተለያዩ ሻንጣዎች ተደርገው ነው በወቅቱ ሊያዙ የቻሉት ሲሉም ተናግረዋል፡፡

እያንዳንዳቸው ሻንጣዎች 541 ኪሎግራም የሚመዝኑ ሲሆን በግምት እስከ 243 ሚሊየን የደቡብ አፍሪካ ራንድ እንደሚያወጡ ነው የተነገረው፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው የኮኬይን ምርት በሀገር ውስጥ ለገበያ የሚቀርብ አልነበረም ያሉት የፖሊስ አዛዡ ወደ አውሮፓ ሀገራት ለማስተላለፍ የተዘጋጀ ነበር ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሄኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *