የበርካቶችን ህይወት እየታደገች የምትገኝው ራፐር እና ዶክተሯ እንስት አድናቆት እየተቸራት ይገኛል፡፡

በመድረክ ስሟ ላዮንስ እየተባለች የምትጠራው ላ ቶያ ሙምቦላ ፣ ቀን ቀን በህክምና ሙያ ፣ ማታ ማታ ደግሞ በመሸታ ቤቶች በራፐርነት ሙያ እየሰራች የምትገኘዋ እንስት በናሚቢያውያን ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት እየተቸራት ይገኛል፡፡

የናሚቢያ ዜግነት ያላት ይሕች የጥምር ሙያ ባለቤት በናሚቢያ ዋና ከተማ ዊንድሆክ በተለያዩ ሆስፒታሎች እና የመዝናኛ ቦታዎች እየተዟዟረች ሰዎች ታክማለች እንደዚሁም ታዝናናለች፡፡

የ27 አመቷ ዶክተር እና ራፐር የኮሮና ቫይረስ በመላው አለም መከሰቱን ተከትሎ አብዛኛውን ጊዜዋ ሆስፒታል ላይ እንደምታሳለፍ ተናግራለች፡፡

“ሰዎች ሲደሰቱ ማየት ያስደስተኛል ፣ለዛም ነው ሁለቱን ዘርፍ በእኩል እያስኬድኳቸው ያለው “ብላለች፡፡

ላ ቶያ በፈረንጆቹ 2015 የመጀመርያ የሙዚቃ ስራዋ ለአድናቂዮቿ የበረከተች ሲሆን ያልተለመዱ እና የማህበረሰቡን ባህል እና አኗኗር ላይ ያተኮሩ ስራዎችን እንደምትወድ ትናገራለች፡፡

አሁን አሁን ሙሉ ስራዬ አድርጌ የያዝኩት ህክምናው ነው ምክንያቱም ሰዎች ጤና ካልሆኑ መዝናናት የሚባል ነገር አይታሰብም ከሁሉ በፊት ጤና ይቀድማል የሚል እምነት እንዳላት ላ ቶያ ተናግለች፡፡

ላ ቶያ እዚህ የመድረሷ ሚስጥር የእናቷ ጽናት እና ጠንካራነት እንደሆነ ተናግራ፣ በየትኛውም ሁኔታ ብንሆን ማንኛውም ነገር መስራት እንደምንችል ለማሳየት ነው ሁለቱን ስራ እየሰራሁ የምገኝው ስትል ተናግራለች፡፡

አልጀዚራ

ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *