ግብፅ በደቡብ ሱዳን ግዙፍ ግድብ ልትገነባ መሆኑን አስታወቀች

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተፅዕኖ ያሳድርብኛል እያለች የምትገኘዉ ግብጽ በደቡብ ሱዳን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉል ግዙፍ ግድብ ልትገነባ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የግብጽ እና የደቡብ ሱዳን የዉሓና መስኖ ሚኒስትሮች ይገነባል ተብሎ የሚታሰበዉን ግድብ ጨምሮ በሌሎች ፕሮጀክቶች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸዉን ኢጂፕት ኢንዴፔንዴንት ዘግቧል፡፡

ግብጽ ይህንን ግድብ የምትገነባዉ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ችግርን ለመፍታት እንዲሁም ለደቡብ ሱዳንና ለአካባቢዉ አገራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጥ ነዉ ተብሎለታል፡፡

በበደቡብ ሱዳን ሲዊ ወንዝ አካባቢ የሚገነባዉ ይህ የግብጽ ዋዉ የተሰኘዉ ግዙፍ ግድብ ብዙ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚያመነጭና ለግማሽ ሚሊዮን ዜጎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገምቷል፡፡

በደቡብ ሱዳን የግብጽ አምባሳደር ጆሴፍ ሞም እና የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ጄምስ ዋኒ ኢጋ ፕሮጀክቱን በተመለከተ በቀጣይ በካይሮ ዉይይት እንደሚደረግባት መናገራቸዉን ዘገባዉ አስፍሯል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተፅዕኖ ያሳድርብኛል ስትል የነበረችዉ ግብጽ አዲስ የምትገነባዉ የዋዉ ግድብ ሊደርስብኝ የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ያግዛል ማለቷ ግርምትን የጫረ ጉዳይ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *