ግዙፍ የቻይና አየር ማረፊያ በይፋ ስራ ጀመረ።

በቻይና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቼንግዱ ቲያንፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በይፋ ሥራውን የጀመረ ሲሆን አየር መንገዱ በመክፈቻ በረራው የመጀመሪያውን ጉዞ ወደ ቤጂንግ አድርጓል ፡፡

በሲቹዋን ግዛት የተገነባው የቼንግዱ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ሻንጋይ እና ቤጂንግን በመቀላቀል በአገሪቱ ሶስተኛ አለም ዓቀፍ አየር መንገድ ሆኗል ፡፡

ወደ 70 ቢሊዮን የቻይና ዩዋን (10.8 ቢሊዮን ዶላር) በሆነ ወጪ የተገነባው ግዙፍ የአቪዬሽን ማዕከል ምዕራፍ አንድ በዓመት እስከ 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው መሆኑ ተነግሯል ፡፡

አየር ማረፊያው በአጠቃላይ 710,000 ካሬ ሜትር ቦታን የሚሸፍን ሲሆን በየአመቱ 120 ሚሊዮን የሚሆኑ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል 1.4 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚሸፍኑ ተርሚናሎችንም ይዟል።

CNN

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *