ቻይና ለጃፓን ማስጠንቀቂያ ሰጠች፡፡

ቻይና ጃፓንን ያስጠነቀቀችዉ አንድ የጃፓን ከፍተኛ ባለስልጣን ታይዋንን “ሀገር” ብለዉ መጥራታቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

በዚህም ቻይና ታይዋን ሀገር ሳትሆን የቻይና አንድ የግዛት አካል ናት በሚል ጃፓን ለጉዳዩ ማብራሪያ እንድታቀርብ እና እርምት እንድታደርግ ጥሪ አቅርባለች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን እንዳሉት የጃፓን ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ያሱሂድ ናካያማ ያደረጉት የተሳሳተ ንግግር የቻይና እና ጃፓን ትስስርና ፖለቲካዊ መሰረት ብሎም በሃገራቱ መካከል ያለውን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ እንዳይከተው መስተካከል ይገባዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የቻይናን ሉዓላዊነት በምንም መንገድ እንዳትዳፈር እና ለ ‹ታይዋን ነፃነት ኃይሎች› ነን ለሚሉ የተሳሳተ መልዕክቶችን ከመላክ እንድትቆጠብ በጥብቅ አስጠንቅቃለች ፡፡

የታይዋን ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት ከቻይና ጋር ለሚያጋጥም የትኛዉም አይነት ጫና ለመቋቋም ወታደራዊ ሃይልን ማጠናከር ይገባል ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡

ዥንዋ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *