የገቢዎች ቢሮ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ግምታቸው ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአጣዬ እና በመተከል ዞን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚሆን ግምታቸው ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የቢሮው የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ተሰባስበው ወደ ስፍራው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ኮማንደር አህመድ አክለውም ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች መደገፊያ የሚሆን እንድናሰባስብ ይጠበቅብን የነበረው በጥሬ ገንዘብ 1 ሚሊዮን ብር በቁሳቁስ ደግሞ 4 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የነበረ ሲሆን ኮሚቴው ለቢሮው ተጠሪ የሆኑ ሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን በማስተባበር ከዕቅዱ በላይ ማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የተሰባሰበውን የዕርዳታ ቁሳቁስ የከተማው አስተዳደር ካዘጋጃቸው የዕርዳታ ቁሳቁሶች ጋር ወደ ስፍራው የማጓጓዝ ስራ ተጀምሯል ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *