ዩጋንዳ ኮቪድን ለማከም የሚውል ከዕፅዋት የተቀመመ መድሀኒት ይፋ አደረገች፡፡

በዩጋንዳ የጤና ቢሮ ሀላፊዎች ይህን በሀገር ውስጥ ከዕፅዋት የተቀመመ መድሀኒት፣ የኮቪድ-19 ህመምተኞችንና ሌሎች የቫይረስ ኢንፌክስኖችን ያክማል ሲሉ አፅድቀውታል፡፡

የዩጋንዳ ብሔራዊ መድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እንደገለፀው፣ ምርቱ የተቀመመው በባህላዊ መንገድ በርካታ በሽታዎችን ሲፈውስ ከነበረ ዕፅዋት ነው፡፡

ባለስልጣኑ ይህን ኮቪዴክስ የተባለ መድሀኒት ያፀደቀው መንግስት ፈቃድ ስላልሰጠው እንዳትጠቀሙ ሲል ህብረተሰቡን ካስጠነቀቀ ከሳምንት በኋላ ነው፡፡

መድሂኒቱን ያገኙት ፕሮፌሰር ፓትሪክ ኦግዋንግ የሚያስተምሩበት ምባራ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመድሀኒቱ ባለቤት እንደሆነ አንስቶ ተገቢውን ሂደት ሳያልፍ ሾልኮ ለገበያ እንደበቃ ሲገልፅ ነበር፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ብሔራዊ የመድሐኒት ባለስልጣኑ ፤ መድሐኒቱን ያፀደቀው፤ በመጀመርያ ግምገማ፣ በታተመ ጥናታዊ ፅሑፍ፣ በደህንነት ጥናት፣ እንዲሁም ኮቪድን ይከላከላልም ያክማልም ሲል የመድሐኒቱ ፈጣሪ በማስረጃ ሳይደግፍ የሰጠውን አስተያየት ተመርኩዞ ነው ተብሏል፡፡

መድሀኒቱ ገበያ ውስጥ የገባው ከበርካታ ወራት በፊት እንደሆነ ይነገራል፡፡

መድሀኒቱ ከ 1 ዶላር በታች ሲሸጥ የነበረ ሲሆን ሁለተኛ ዙር የወረርሽኝ ስርጭት ሲከሰት ግን የመድሀኒቱ ዋጋ እስከ 22 ዶላር መሸጥ ጀምሯል፡፡

ዩጋንዳ በሰኔ ወር መጀመርያ በሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸዉን የሚያጡ ሰዎች ሲበራክቱ እና ሆስፒታሎች በተጠቂዎች ሲጨናነቁ ከቤት ያለመውጣት መመርያ (lockdown) ጥላለች፡፡

ከ 850 ሺህ በላይ ዩጋንዳውያን የኮቪድ ክትባት የተከተቡ ሲሆን ለጤና ባለሙያዎች፣ለመምህራን፣ዕድሜያቸው ለገፉ አረጋውያን እና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ቢቢሲ

በሔኖክ አስራት
ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *