የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በ 2020/21 የበጀት ዓመት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

ባንኩ በ2020/21 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 2 ነጥብ 39 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ካለፈዉ ዓመት አንፃር 42.26 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡

ይህም በባንኩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 2.39 ቢሊዮን ብር (ከፕሮቪዥን እና ዲፕሪሴሽን በፊት) ማትረፍ መቻሉን የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ ደርቤ አስፋው በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡

ባንኩ ካገኘው ትርፍ ባሻገርም በ 2012 ዓ.ም ከነበረዉ 52.92 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሃብት የ28.62 ቢሊዮን ብር ጭማሪ በማሳየት በ2013፣ 81.54 ቢሊዮን ብር ማድረሱንም አቶ ደርቤ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 72.69 ቢሊዮን ብር ማድረሱንም ባንኩ ያስታወቀ ሲሆን እንዲሁም የደንበኞቹን ብዛት 7.73 ሚሊዮን ማድረሱንና በዓመቱ 49 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት የቅርንጫፍ ብዛቱን ወደ 469 ከፍ ማድረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠን 56 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ያስታወቁት የባንኩ ፕሬዝደንት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 4.65 ቢሊዮን ብር መድረሱንና ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ሲነፃፀር የ55 በመቶ ብልጫ ማሳየቱንም ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *