በኢትዮጵያ 5 መቶ ወረዳዎች በባንክ አገልግሎት ተደራሽ አልሆኑም፣ 60 በመቶ ዜጎችም መብራት አያገኙም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚንስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

የአገሪቱን የዋጋ ንረትና የባንክ ዘርፉን በተመለከተ በአገሪቱ 5 መቶ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት የላቸውም ብልዋል።

አሁን ላይ በአገሪቱ የተለያዩ ባንኮች ከ7 ሺህ በላይ ቅርንጫፎች ቢኖራቸውም አሁንም ድረስ ግን በርካታ ዜጎች የዘርፉ ጠቃሚ አይደሉም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከሁለት አመት በፊት 38 ሚሊየን ዜጎች የባንክ ደብተር የነበራቸው ሲሆን አሁን ላይ ግን 66.2 ሚሊየን ዜጎች የባንክ ደብተር አላቸው ብለዋል።

መብራትን በተመለከተም 60 በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ድረስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አይደለም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በቀጣይ የሃይል አቅርቦትን በማስፋት እነዚህን ዜጎች የዘርፉ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የዋጋ ንረትን በሚመለከት ፣ኮቪድ 19 ፣አንበጣ ፣ጎርፍ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ የፕሮጀክቶች መጓተት ፣የአለም ገበያ መናር እና በውጭ አገራት የሚኖሩ ዜጎቾ ወደ አገራቸው መመለሳቸው በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳሳደርም ዶ/ር አብይ አህመድ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.