ባለስልጣናት ያለ አግባብ የሚያባክኑት ሃብት መቆም አለበት፡፡

በአንዳንድ ክልሎች ላይ በሚሊሻ የሚታጀብ አመራር አለ ይሄም ተገቢ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አህመድ አስታውቀዋል፡፡

ሹመኛ ማለት ሰው ማንጋጋት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይልቁኑም ህዝብን ለማገልገል እድሉን ያገኙ የመንግስት ሃላፊዎች የሚጠበቅባቸው ሃላፊነት በሚገባ መወጣት ይሮርባቸዋል እንጂ የህዝብን ሃብት ያለአግባብ ማባከንና ያልተገባ ወከባ መፍጠር እንደሌለባቸው አሳስበዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ መሰረተ ልማት ላይ በክልሎች ያለው ተደራሽነት ፍታሃዊነት አለው ወይ የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡

በክልሎች በተለየ መልኩ የሚበጀት ፍትሃዊ ያልሆነ በጀት የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይልቁኑም በጀት ብቸኛ የልማት መደገፊያ ያለመሆኑንና በየአካባቢው ተዝቆ የማያልቅ ሃብት መኖሩን እና ያንን ሃብት የመጠቀም ሁኔታ መኖሩ ሊታወቅ እንደሚገባ አሰታውቀዋል፡፡

በየክልሉ የሚበጀተው በጀት ብቻ ሳይሆን ክልሎች ያላቸውን ሃብት በመጠቀም የሚያመጡት የልማት ውጤት በክልሎች ያለውን የመልማት አቅም ይወስነዋል ያሉት ዶ/ር አብይ ለዚህ ደግሞ አመራሮች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በማንሳት፣ ነገር ግን ይሄ መሆን ሲገባው አንዳንድ ባለስልጣናት ባልተገባ መልኩ የሚያባክኑት ጊዜና ሃብት በህዝብ ላይ ተፅእኖ እንደሚያሳድርና ብልፅግናንም የሚያመጣ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

የውልሰው ገዝሙ

ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *