ሳፋሪኮም በኢትዮጲያ ለሚከፍተው ቢሮው አንዋር ሶስን ሀላፊ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።

ኩባንያው ከዚህ ቀደም በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ የድርጅቱ ዳይሬክተር ሆነው ይሰሩ የነበሩትን አንዋር ሶስ የተባሉትን ግለሰብ ከሰኔ 24 2013 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጲያውን ቢሮ እንዲያስተዳድሩ መመደቡን ዛሬ አስታውቋል።

አዲስ የተሾሙት ሀላፊ ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለውና የስድስት ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ተቋም እንደሚመሩ መመደቡን ነው ያስታወቀው።

አንዋር በቢዝነስ አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአሜሪካ የግሪክ ኮሌጅ (ዴሬ) እንዲሁም በካናዳ ሞንትሪያል ከሚገኘው ኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲቲ በማስተርስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙና የግሪክ ዜግነት ያላቸው መሆኑም ታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *