በሩሲያ በረራ ላይ የነበረ አዉሮፕላን መሰወሩ ተነገረየአገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀዉ ኤ ኤን 26 የተሰኘዉነወ 28 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረዉ አዉሮፕላን ደብዛዉ ጠፍቷል ብሏል፡፡

አዉሮፕላኑ ከፔትሮፓቭሎቭስኪ ተነስቶ ወደ ካምቻትካ ልሳነ ምድር በረራ ላይ እያለ ከ ራዳር መዉጣቱን አልጄዚራ የአገሪቱን መንግስት ጠቅሶ ዘገቧል፡፡

የሩሲያ የአገር ዉስጥ የትራንስፖርት ቃል አቀባይ ቫሌንቲና ግላዞቫ፤ አዉሮፕላኑን የመፈለጉ ስራዉ እየተከናወነ ነዉ ብለዋል፡፡

በአዉሮፕላን ዉስጥ ስድስት የበረራ ሰራተኞች፤ አንድ ህጻንን ጨምሮ 22 ተሳፋሪዎች በድምሩ 28 ሰዎች እንደነበሩም ዘገባዉ አስታዉቋል፡፡

ከአካባቢዉ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አዉሮፕላኑ ወደ ባህር ሳይሰጥም አልቀረም እየተባለ ነዉ፡፡

በሩሲያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአዉሮፕላን አደጋዎች እየተበራከቱ መምጣታቸዉንም ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ

ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *