የአሜሪካን ጦር ኃይል እርጅናን የሚያስቀሩ መድሃኒቶችን ሊሞክር እንደሆነ ተሰማ

በቴክኖሎጂ በተራቀቀው በዚህ ዘመን ከወደ አሜሪካንም ተመራማሪዎች ለወትሮ በፊልም ላይ የምናውቀውን ሳይንሳዊ ግኝት እውን ለማድረግ በመንደርደር ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

በአሜሪካን ጦር ኃይል ስር የሚገኘው የልዩ ተልእኮ እዝ (SOCOM) ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት አንስቶ እርጅና በወታደሮቹ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕንዖ ያጠፋሉ የተባለላቸውን ኪኒኖች መሞከር እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የሰው ልጆችን አካላዊ አቅም የማሳደግና ወታደሮችንም ጤናማና ለረጅም ጊዜያት በከፍተኛ ብቃት እንዲያገለግሉ የማድረግ አላማያለው ነው ተብሏል፡፡

ኪኒኖቹ ስራቸውን የሚሰሩት ከሰው ልጅ እርጅና እና የአካል ብቃት መውረድ ጋር የሚያያዘውን ኒኮቲናማይድ አዴኒን ዲኒውክላታይድ (NAD+) የተሰኘ ኮኤንዛይም በማጠናከር ነው፡፡

የልዩ ተልእኮ እዙ ታድያ በወታደሮቹ የሰውነት ስርዓት ውስጥ ተጨማሪ ኒኮቲናማይድ አዴኒን ዲኒውክላታይድን በማከል ከዕድሜ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ለመቀነስ ብሎም አካላዊና አዕምሮአዊ ዝግጁነትን በማሻሻል በእድሜ ብዛት እየቀነሰ የሚመጣ የወታደሮች ብቃት መውረድን ለመከላከል አቅዷል፡፡

እንደ እዙ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ሊሳ ሳንደርስ ምልከታ ሙከራው ስኬታማ የሚሆን ከሆነ እርጅናን በማዘግየትና በእድሜ አመሻሽ ላይ የሚከሰት ጉዳትን በመቀነስ የሚያስደንቅ ልዩነት ፈጣሪ ይሆናል፡፡

ምንጭ፤ Futurism

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በዳዊት አስታጥቄ

ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *