የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2013 በጀት አመት ከ401 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ 2013 በጀት ዓመት፣ በአዲስ- አዳማ እና በድሬዳዋ- ደወሌ የክፍያ መንገዶች በአጠቃላይ 401 ሚሊዮን 4 ሺህ 247.65 ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጿል፡፡

ገቢው የተገኘው ከክፍያ መንገድ አገልግሎት እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች (ከማስታወቂያ ቦታዎች ኪራይ፣ ከወደሙ የመንገድ ሃብቶች ካሳ ክፍያ፣ ከተሽከርካሪ ማንሻና መጎተቻ መሰል ክፍያዎች) መሆኑን ተገልጿል፡፡

የመንገዱን ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያ በተለያዩ ቦታዎች ሰፊ የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት፤ በማስተማር እና አደጋ በሚያጋጥም ጊዜም የአደጋ መቆጣጠሪያ እና የጉዳት መቀነሻ መለኪያዎች መሰረት በማድረግ ፤ በደረሰ አደጋ የተዘጉ የመንገድ ክፍሎችን በፍጥነት ክፍት በማድረግ የትራፊክ ፍሰት እንዲቀጥል ማድረግ ተችሏል ነዉ ያለዉ፡፡

በየጊዜው የሚያጋጥሙ የትራፊክ አደጋዎች ፤ለመንገዱ ጥገና የሚውሉ የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት ፤በድረደዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ ላይ የሚስተዋለው የወደብ እቃዎችን ከክብደት በላይ ጭኖ መንገዱን መጠቀም ዋነኛ ችግሮች መሆናቸውን ኢንተርፕራይዙ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *