የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በተሳሳተ መንገድ ተተርጎሞ ነው እንጂ ኢትዮጵያ በኬኒያ ያላትን ኤምባሲ አይዘጋም ሲሉ አምባሳደር መለስ አለም ተናገሩ

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለሰ አለም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሳምንቱ መጀመሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት መልስ እና ማብራሪያ ወቅት ከሚዘጉ ኤባሲዎች መካከል የኬኒያው ኤምባሲ እንደሚገኝ ተናግረዋል መባሉ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጲያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በቀጠናዊ ውህደት ዙሪያ ለሚካሄደው ጠንካራ ስራ አጋር የሆነው በኬንያ ያለው ተልእኮ እንደማይዘጋ አቶ መለስ አለም ገልጻዋል ፡፡

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት ምሳሌ እንጂ እውነት ኤምባሲው ይዘጋል ማለታቸው አይደለም” ብለዋል፡፡ “በውጭ ፖሊሲያችን ለጎረቤቶቻችንን ቅድሚያ የሚሰጥ በመሆኑ ኤንባሲው አይዘጋም ” ሲሉ ኔሽን ለተባለው የኬኒያ እለታዊ ጋዜጣ አብራርተዋል ፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በኋላ ኤምባሲው በኬንያ ያለው ተልዕኮው ያበቃል ተብሎ የተናፈሰው ወሬ “የሐሰት እና መላምት ” ነው ብለዋል፡፡

“የናይሮቢ ተልእኮ አይዘጋም እንደ ኬንያ ያሉ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገሮች ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቀዳሚ ሆነው ቆይተዋል አሁንም ያ ነው የሚዘልቀው ”ነው ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት በሰጡት ማብራሪያ ፣ ኢትዮጵያ ወጪዎችን ለመቀነስ በርካታ ኤምባሲዎችን እንደምትዘጋ እና አብዛኞቹ ዲፕሎማቶች ወደ ሀገራቸው ተመልሰው እንደሚሰሩ ተናግረው ነበር ሲል ዘገባው አስታውሷል፡፡

“ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 60 ወይም ከዚያ ያህል ኤምባሲዎች እና ቆንጽላዎች ሊኖሯት አይገባም የአሜሪካን ዶላር በየቦታው ከመጣል ይልቅ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ኤምባሲዎች መዘጋት አለባቸው”ብለዋል፡፡

ነገር ግን መዘጋት አለባቸው የተባሉት ኤምባሲዎች የትኞቹ እንደሆኑ በዝርዝር አልተገለጹም ፡፡

አክለውም “ለምሳሌ በኬንያ ያለው የኢትዮጵያ አምባሳደር ምናልባትም በዓመት አንድ ጊዜ ወይም በሁለት ዓመት ውስጥ ከኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ይገናኛሉ” ብለዋል ፡፡

ብልጽግና በይፋ ምርጫውን ማሸነፉ ከተረጋገጠ ፣ፓርቲያቸው ፖሊሲውን ተግባራዊ እንደሚደርግ ጠቁመዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔአበባ ሻምበል

ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *