በማሳጅ ቤት ስም የወሲብ ንግድ የሚሰሩ ቤቶች ሊታሸጉ ነው፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለማሳጅ አገልግሎት ተብለው የተከፈቱ ቤቶች የወሲብ ንግድ ላይ ሰማርተው ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በከተማዋ በርካታ የማሳጅ ቤቶች ከህግ ውጭ የሆነ ስራ ላይ መሰማራታቸውን አስታውቋል፡፡

የፖሊስ ኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ ኮማደር ፋሲካ ፋንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በማሳጅ ስም የወሲብ ንግድ የሚሰሩ ቤቶች እየተበራከቱ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ኮማደር ፋሲካ ከሆነ ሊገመቱ የማይችሉ ቤቶችም በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ነው የተናገሩት፡፡

ፖሊስ ኮሚሽኑ በከተማዋ በበርካታ አካባቢዎች ጥቆማ እየደረሰው መሆኑን ጠቅሶ የመለየት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ነው ያስታወቀው፡፡

በከተማዋ ይህ ጉዳይ በውል ከሚስተዋልባቸው ሰፈሮች መካከል ቦሌ መንገድ ውስጥ ለውስጥ አትላስ አካባቢ ቺቺኒያ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር እንደዚሁም 22 አካባቢ ችግሩ በብዛት የሚስተዋልባቸው ቦታዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ማሳጅ ቤት ተብለው የተከፈቱት ቤቶች አብዛኛዎቹ ቀን ላይ ስራ እንደማይሰሩ የተነገረ ሲሆን ምሽት ምሽት ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አንዳንዶቹ ማሳጅ ቤቶች የሱስ ማዘውተሪያ የሆኑበት አጋጣሚም እንዳለ ነው ኮማንደር ፋሲካ የተናገሩት፡፡

በእነዚህ ቤቶች ላይ የተጀመረው የማጣርት ስራ ሲያልቅ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.