ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ ውጤታማ መሆኑ፣ ከተለያዩ ወገኖች ሲሰነዘሩ የነበሩት ተቺዎችን በሙሉ ውድቅ ያደረገ ነው ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ላውረንስ ፈሪማን ተናገሩ፡፡
ፊሪማን ኢትዮጵያዊያን ያካሄዱት 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ምን ያህል ለዲሞክራሲ መጎልበት ፍላጎት እንዳላቸው ያሳዩበት ነበረም ብለዋል፡፡
ምእራባውን ሚዲያዎች እና መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ የነበራቸው የተዛባ አመለካከት የቀየረ ከመሆኑም ባሻገር የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ሂደት የጠቆመ ነው ብለዋል፡፡
ላውረንስ ፈሪማን በትንታኔያቸው እንደ ማሳያ የተጠቀሙት የአፍሪካ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን ያወጣውን መረጃ ነው፡፡
የህብረቱ ታዛቢ ቡድን ምርጫው አንዳንድ እጥረቶች የነበረበት ቢሆንም እጅግ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሂደቱ የጠበቀ እንደነበረ አስታውቋል ያሉት ተንታኙ ይህም በምእራባዊያን ዘንድ ተቀባይነት ያላገኝ ጉዳይ እንደሆነም ነው ላውረንስ የተናገሩት፡፡
አሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ ሀገራት ኢትዮጵያን ማመስገን እና እንኳን ደስ አለሽ ሊሉ ይገባ ነበር፣ ሆኖም ዝምታ ነው የመረጡት፣ ይህ የምርጫው ውጤታማነት የሚገልጽ ነው ሲሉ ነው ሀሳባቸውን የገለጹት፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ላከናወነው ትልቅ ተግባር የውጭ ሀገራት ምስጋና ማቅረብ የነበረባቸው ቢሆንም ወንጪት ሰባሪነታቸው በግልጽ አሳይተዋል እናም በሀገሪቱ የፈጠሩት ሁሉ የሀሰት መሆኑ ሊገባቸው ይገባል ብለዋል ላውረንስ ፍሪማን፡፡
ከምርጫው በፊት እና ከምርጫው በኃላ ስለ ኢትዮጵያ የውሸት ዜናቸውን ሲያሰራጩ የከረሙት የምእራባውን ሚዲያዎች አሁን በሌላ የውሸት አጀንዳ ተጠምደዋል ይህ የሚያሳየው ደግሞ የሀገሩቱ ጠላት መሆናቸው ነው ብለዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም











