የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር 20 ቤቶችን የማደስ ስራ ዛሬ ጀምሯል፡፡

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያደርገዉን የ20 ቤቶችን እድሳት ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል በዛሬዉ እለት አስጀምረዋል፡፡

የቤቶቹ እድሳት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የተገለፀ ሲሆን የ10 ቤቶች እድሳት ሙሉ ወጪ በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንደሚሸፈን ሰምተናል፡፡

ቀሪ 10 ቤቶች ደግሞ ናሽናል ሲሚንቶ ፣ዳንጎቴ እና ሌሎች የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እንደሚሸፍኑ የሚኒስቴር መስርያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አበባ ታመነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሯ ወ/ሮ አበባ እንዳሉት፣ ቤቶቹ በተባለላቸው ቀን እንደሚጠናቀቁና የቤቶቹ እድሳትም ቤቶቹ በነበራቸው ካሬ ልክ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡

ባለ ሁለት ፎቅ እንድሚሰራና የምድር ቤቶች ለንግድ እንደሚውሉ እንዲሁም እየሰሩበት ራሳቸውን እንዲለውጡ የሚደረግበት እንደሚሆን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

እድሳቱ እስከሚጠናቀቅም በአካባቢው የሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ ማረፋቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ታዝቧል።

በረድኤት ገበየሁ

ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *