ግልጽ ጉድለቶችን የምትፈፅሙ አሽከርካሪዎች መኪናችሁን እስከ ማቆም የሚደርስ ቅጣት ይጣልባችኋል ተብላችኋል

በክረምት ወቅት የሚከሰተውን ትራፊክ አደጋ ለመቆጣጠር የክረምት ጊዜ እቅድ መዘጋጀቱ ተነገሯል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ማኔጅመት እና የአዲስ አባበ ፖሊስ ኮሚሽን እና ሌሎችም ተቋማትን ያሳተፈ እቅድ መውጣቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እቅዱ ሙሉ በሙሉ በክረምት ጊዜ የሚከሰቱትን የትራፊክ አደጋዎች ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

አሽከርካሪዎች ግልጽ ጉድለቶች የሚባሉት ልክ እንደ እስፖኪዮ፣ ቦሎ፣ የታርጋ ቁጥር ግልጽ ያለመሆን፣ እና ሌሎችም ቴክኒካዊ ጉድለቶች ከፈጸሙ መኪናቸው እስከ ማቆም ቅጣት እና መንጃ ፈቃዳቸው እስከ መንጠቅ የሚደርስ ቅጣት ይጣልባቸዋል ተብሏል፡፡

ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት አሽከርካሪዎች ከቅጣት እራሳቸውን እንዲያድኑ እና የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማሟላት አለባቸው ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.