100 ዜጎች በእሳት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በ2013 በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች 100 ዜጎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተገለጸ፡፡ከዚህ በተጨማሪም 135 ያህል ሰዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባለዋል ተብሏል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበጀት አመቱ 538 ያህል አደጋዎች መከሰታቸውን አስታውቋል፡፡ከደረሱት አደጋዎች ውስጥ 385 ያህሉ የእሳት አደጋዎች ሲሆኑ 153 ደግሞ ከእሳት አደጋ ውጪ የሆኑ ድንገተኛ አደጋዎች ናቸው ተብሏል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ በአደጋዎቹ ምክንያት ከ355ሚሊየን ብር በላይ በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ሲል ነው ኮሚሽኑ ያስታወቁት፡፡

እንደዚሁም ከአምስት ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከጉዳት ማዳን ተችሏል ብለዋል፡፡

ከደረሱት የእሳት አደጋዎች አብዛኛዎቹ መንስኤያቸው የኤሌክትሪክ ኮንታክት እንደሆነ ነው አቶ ጉልላት የተናገሩት፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *