ለሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻና ምርመራ እንደሚደረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ለትግራይ ክልል ለሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ የአለም አቀፍ ተቋማት የበረራ ፍቃድ ቢሰጥም፤ እያንዳንዱ በረራ ግን መነሻው ከአዲስ አበባ እንደሆነም ተገልጿል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን፣ ለሰብዊ እርዳታ በሚል ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል ።

እያንዳንዱ በረራ አዲስ አበባ ካለፈ በኋላ ወደ ትግራይ እንደሚሄድ የገለፁት አምባሳደር ዲና፣ሲመለሱም አዲስ አበባ አርፈው መሄድ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ

ሐምሌ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *