በእያንዳንዱ ደቂቃ 11 ሰው በርሃብ ምክንያት ህይወቱ እንደሚያልፍ አንድ ሪፖርት አመለከተ።

በአለም አቀፍ ደረጃ 155 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ያልተረጋገጠላቸው እንደሆነና በእያንዳንዱ ደቂቃ 11 ሰዎች ህይወታቸው እንደሚያልፍ ኦክስፋም የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ይፋ አድርጓል።

ይህ ቁጥር ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸርም 6 እጥፍ መጨመሩ አስደንጋጭ ቢሆንም በጣም ከባድ የሚባል ህይወት እየመሩ ያሉ ሰዎች መኖራቸው መታሰብ ያለበት ጉዳይ እንደሆነም ጥናቱን ያደረገው የኦክስፋም አሜሪካ ፕሬዝደንት ፤ አቢ ማክስማን ተናግረዋል።

ጦርነት ያለባቸው ሀገራት ለከፋ ርሀብ ከሚጋለጡት መካከል እንደሆኑ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ኦክስፋም 20 በጎ አድራጎት ድርጅቶች ተጣምረው ያቋቋሙት መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ድህነት ቅነሳ ላይ የሚሰራ ድርጅት እንደሆነ ከአልጀዚራ ዘገባ ተመልክተናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

መቅደላዊት ደረጄ

ሐምሌ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *