ከሳውዲ አረቢያ ከ21ሺህ በላይ ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

እስካሁን 21ሺህ 1መቶ 82 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ መመለስ እንደተቻለ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታውቀዋል።

ዜጎችን ወደ አገራቸው በማስመለስ ሂደት 99 በረራዎች የተደረጉ ሲሆን ከተመላሽ ዜጎች መካከል 3ሺህ 8መቶ 6 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ 1ሺህ 1መቶ 60ዎቹ ደግሞ ህፃናት ናቸው ተብሏል።

በሳውዲ የተለያዩ ከተሞች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያ ላይ እየደረሰ ያለውን እስርና እንግልት ተከትሎ ኢትዮጵያ ዜጎቿን የማስወጣት ስራ መጀመሯ ይታወሳል ።

በየቀኑም በርካታ ዜጎች ወደ አገራቸው እየገቡ እንደሆነ አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።በአጭር ጊዜ ውስጥም በሳውዲ የሚገኙ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ የማስወጣት ስራው ይጠናቀቃል ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ።

በሳውዲ አረቢያ ከ 40 ሺህ በላይ ዜጎች በችግር ላይ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወቃል።

እነዚህ ዜጎች ለብዙ እንግልትና ስቃይ የተዳረጉ ሲሆን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በትናንቱ የፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ፤ የህዳሴ ግድቡ በድህነታችን ምክንያት በስደት ባሉበት አገር፣ በባዶ እግራቸው እየተባረሩ ላሉም ዜጎች መፍትሔ ያመጣል ማለታቸው ይታወሳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ

ሐምሌ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *