“ግብፅና ሱዳን የቀራቸዉ ኢትዮጵያን ፈጣሪ ጋር መክሰስ ብቻ ” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ የፀጥታዉ ምክርቤት ትናንት ባካሄደዉ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት እንዳስመዘገበች ጠቅሰዉ ፤ ከዚህ በኋላ ጉዳዩ ለምክር ቤቱ የሚቀርብበት ምክንያት የለም ብለዋል፡፡

ግብፅና ሱዳን በህዳሴዉን ጉዳይ ከሶስትዮሽ ድርድር በተደጋጋሚ በመዉጣት የፖለቲካ ቅርፅ እንዲይዝ እስከ ፀጥታዉ ምክር ቤት ሄደዋል ምናልባት የቀራቸዉ ፈጣሪ ጋር መሄድ ብቻ ነዉ ሲሉም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

“አሁን የቀራቸዉ ኢትዮጵያን ፈጣሪ ጋር መክሰስ ብቻ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከዚህ በኋላም ግን የእነ ግብፅ ሥራ መሆን ያለበት እንቦጭን በመከላከል የአባይን ህልዉና ማስጠበቅ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ትናንት ምሽት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ተወያይቶ ጉዳዩ በአፍሪካ ህብረት በኩል መሄድ ያለበት የልማት አጀንዳ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል፡፡

ይህንንም ሀሳብ በርካታ የምክርቤቱ አባል አገራት የደገፉት ሲሆን የእነ ግብፅ እና ሱዳን ሴራንም ኢትዮጵያ ያከሸፈችበት ምሽት መሆኑን በርካቶች በመናገር ላይ ናቸዉ፡፡

የዉሃ፤ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለም የኢትዮጵያን አቋም ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በተገቢዉ መንገድ አስረድተዋል ብለዋል፡፡

እናም ግብፅም ሆነች ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ የሚያቀርቡትን የተሳሳተ ክስ ወደ ጎን በመተዉ የአባይን ተፋሰስ በማልማት በተለይም እንቦጭን በማስወገድ ሥራዉ ላይ ርብርብ ሊደርጉ ይገባል በማለት አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *