ቡድኑ እንዳስታወቀዉ ከዚህ በኋላ ቤጂንግ በአፍጋኒስታም ምድር በኮንስራክሽን ዘርፍ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የታሊባን ቃል አቀባይ ሱሃይል ሻይን ሲናገሩ፤ ቻይና በጦር በፈራረሰቸዉ አፍጋን ምድር በኮንስትራክሽን ግንባታ ላይ መሳተፉ ፍላጎት ካላት ቡድኑ አስፈላጊዉን ከለላ ያደርጋል ነዉ ያሉት፡፡
ቻይና ወዳጃችን ነች ያለዉ ቡድኑ የእሷን ሰላም መሆን እንፈልጋለን፤በቀጣይም በኢንቨስትመንት እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ እንድትሰማራ እገዛ እናደርጋለን ብሏል፡፡
ይህ የታሊባን ጥሪ የአሜሪካ እና የአጋሮቿ የጦር ሃይል ከ20 አመት በኋላ አፍጋኒስታንን ለቆ መዉጣቱን ተከትሎ እንደሆነም አናዶሎ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
የአፍጋንን ምድር ተጠቅመዉ በሌሎች አገራት ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚመኙ አገራትም ከዚህ በኋላ ወደ አገሪቱ ድርሽ አይልም ሲሉ ቃል አቀባዩ አስታዉቀዋል፡፡
የአሜሪካ ጦር ከአፍጋን መዉጣቱን ተከትሎ ታሊባን በርካታ ግዛቶች እየተቆጣጠረ እንደሚገኝና በዚህም የፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋሃኒ መንግስት ዉጥረት ዉስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 06 ቀን 2013 ዓ.ም











