ኢትዮ ቴሌኮም በ2013 በጀት አመት 56.5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አሳወቀ

የኢትዮ ቴሌኮም 2013 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየተሰጠ ነው።

በተያዘው በጀት አመትም 101.7 በመቶ ያሳካን ሲሆን 56.5 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝተናል ብለዋል። ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 18.4 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል።

በዚሁ አመት የደንበኞች ብዛት 56.2 ሚሊየን መድረሱን የተናገሩ ሲሆን ይሄ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸርም 22 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

የሶስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ቀርጾ እየሰራ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም በ2010 ዓ.ም 37.92 ሚሊየን ደንበኛ የነበረው ሲሆን እየተጠናቀቀ ባለው አመት 56.2 መድረሱን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በመግለጫቸው አንስተዋል።

ከውጭ የስልክ ጥሪዎች ደግሞ 166.5 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱም በመግለጫቸው ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በየአመቱ ገቢውን ሲያሳውቅ እንደሚያደርገው ሁሉ ዘንድሮም የሶስት ቀን የምስጋና ነፃ አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቋል

በዚሁ መሰረት 1GB ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎትና እና የድምፅ፣የኢንተርኔት እና የመልዕክት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል 303 ፍሌክሲ ፓኬጅ ነው ለሶስት ቀና በነጻ የተሰጠው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

መቅደላዊት ደረጄ

ሐምሌ 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.