የመጀመሪያውን ዙር ክትባት የወሰዱ ዜጎች ከነገ ጀምሮ ሁለተኛ ዙር ክትባታቸውን መውሰድ ይጀምራሉ

የመጀመሪያው ዙር የኮሮና ቫይረስ ክትባትን የወሰዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከነገ ሃምሌ 7 / 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ወደ ጤና ተቋማት ሄደው መውሰድ እንደሚችሉ ጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

በክልሎች ደግሞ ከአርብ ሃምሌ 9 ጀምሮ ሁለተኛ ዙር ክትባቱ መሰጠት እንደሚጀምር ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እንደወሰዱ የተናገሩት ሚኒስትሯ በቀጣይም ቀሪ የህብረተሰብ ክፍሎች የክትባቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የክትባት አይነቶች ተመርተው ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሆነ ያስታወሱት ሚኒስትሯ እነዚህ ክትባቶች ተመሳሳይ የመከላከል አቅም እንዳላቸው ገልፀዋል።

የአፍሪካ ህብረትን እና ሌሎች አጋር ተቋማትን በማቀናጀት ከነሃሴ ወር ጀምሮ ከፍ ያለ መጠን ያለው ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ እንደሚገኝ ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ረድኤት ገበየሁ

ሐምሌ 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.