የጋና ቀዳማዊት እመቤት እስከዛሬ የወሰድኩትን አበል ካልመለስኩ እያሉ ነው

ባለፈው ሳምንት የጋና ፓርላማ ፤ ከማንኛውም ስኬታማ መሪ በስተጀርባ ሚስቶቻቸው አሉ በሚል መነሻ ፤ የፕሬዝዳንቱና የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሚስቶች ደሞዝ እንዲቆረጥላቸው ሲል አፅድቆ ነበር፡፡

በዚህ የፓርላማ ውሳኔ ህዝቡ ተበሳጭቶ ቁጣውን እየገለፀ ነው፡፡

በዚህ የህዝቡ ተቃውሞ ፤ ያዘኑት ቀዳማዊት እመቤቷ ፤ ደሞዙም ይቅርብኝ ፣ ባለቤቴ ስልጣን ከያዘቡት እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2017 ጀምሮ እስካዛሬ የወሰድኩትን አበልም እመልሳለሁ ብለዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤት ሬብካ አኩፎ አዶ ፤ በጭራሽ በፓርላማ የጸደቀውን ደሞዝ አልቀበለውም ያሉ ሲሆን ለ4 አመታት በአበል መልክ የተሰጠኝንም 151 ሺህ 618 ዶላርም ለመመለስ ወስኛለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቀድሞ ነገር እኔ እንዲከፈለኝ አልጠየኩም የሚሉት ቀዳማዊ እመቤቷ አበሉም ቢሆን በይፋ አይሁን እንጂ የመሪ ሚስቶች ሲከፈላቸው የኖረ ነው ብለዋል፡፡

ብሩን ለመመለስ የወሰንኩት ፤ በተንሰራፋው አፍራሽ የጥላቻ አመለካከት ነው ያሉ ሲሆን እኔ ጥቅመኛ ፣ ለተራው ለህዝብ ችግር የማላስብ፣ ራስ ወዳድ ተደርጌ መቅረቤ ቅር አስብሎኛል በማለት የተሰማቸውን በቅሬታ ገልፀዋል፡፡

የፓርላማ ኮሚቴ ባቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት ፤ ፓርላማው የፕሬዝዳንትና የምክትል ፕሬዝዳንት ሚስቶች ለባሎቻቸው ለሚሰጡት ድጋፍ በወር 3500 ዶላር ደሞዝ እንዲከፈላቸው ነው ባለፈው ሳምንት የወሰነው፡፡ደ

ሞዛችሁ ጥንቅር ብሎ ሊቀር ይችላል፣ እስከዛሬ ትከፍሉኝ የነበረውን አበልም እመልሳለሁ ሲሉ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በሔኖክ አስራት

ሐምሌ 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.