ለውጡ የቀየረው የሲቪል ድርጅቶች አዋጅ በሶስት አመት ከ 1500 በላይ ድርጅቶች መመዝገብ ምክንያት ሆኗል ተባለ

ኢትዮጵያ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ከ 1532 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መመዝገቧን ገለጸች፡፡

አንድ ሺህ የሚጠጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሶስት አመት ውስጥ ለመመዝገባቸው ዋነኛ ምክንያት የሲቪል ድርጅቶች አዋጅ መቀየሩ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ በፊት የነበረው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በአዋጅ 621/2001 ተቋቁሞ እስከ የካቲት 2011 አመት ምህረት ድረስ ሲያገልግል ቆይቷ፡፡

አዋጁ በህገ መንግስት የተቀመጠውን የዜጎች የመደራጀት መብት በተሟላ ሁኔታ ያላከበረ እና በአፈጻጸሙም በርካታ ክፍተቶች የነበሩበት እንደነበረ ነው የተገለጸው፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዋና ዳሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደተናገሩት ነባሩ አዋጅ ሙሉ በሙሉ ተሽሮ በአዋጅ 1113/2011 በአዲስ መልክ ጸድቆ ስራ ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ በርካታ የሲቪል ድርጅቶች ፍላጎታቸው ጨምሯል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በነዚህ አመታት ሀገሪቷ 1ሺህ የሚጠጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መመዝገብ መቻሏን ተናግረዋል፡፡

ድርጅቶቹም በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረው ባሳለፍነው 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ እና በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ዋና ዳሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ባጠቃላይ 3336 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይገኛሉ፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *