ሲሚንቶ ከዛሬ ጀምሮ በነፃ ገበያ ስርዓት እንዲገበያይ ተወሰነየሲሚንቶ ግብይትን የሚወስነው እና በንግድና ኢንዱስትሪ ተግባራዊ ሲሆን የቆየው መመሪያ መሻሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የንግድና እቃዎች ጥናትና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰ ጊዜ ሲሚንቶ በነፃ ገበያ ስርዓት እንዲገበያይ ተወስኗል።

ለዚህም ዋና ምክንያት ክረምት በመሆኑ የግንባታ ስራዎች ስለሚቀንስና ከሱ ጋር ተያይዞ የሲሚንቶ ምርት ፍላጎት ስለሚቅንስ እንዲሁም ከፋብሪካዎች ጋር ችግሩን ለመፍታት ስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሲሚንቶ ምርት እጥረት እንዳይኖር መንግስት ከውጪ ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቁና ፋብሪካዎች ምርታቸው እንዲጨምር በመደረጉ መሆኑን አቶ ካሳሁን አብራርተዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *