አሜሪካ በግብፅ ያለው የሰብአዊ መብት አያያዝ አሳስቦኛል አለች

አሜሪካ ግብፅ ላይ ያለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ አሳሳቢ ነው ስትል ገለፀች፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ፤ ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና የበጎ አድራጎት ድርጅት መሪዎች እስር፣ እንግልት ፣ የተለያዩ አይነት ጥቃቶች እና ውክቢያ እየደረሰባቸው ነው ብለዋል፡፡

አሜሪካ በአለም ላይ ካሉ ደፋር የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ጠበቆች፣ እንዲሁም ጋዜጠኞች ጎን ትቆማለች ያሉ ሲሆን ሁሉም ህዝብ የፖለቲካ አመለካከቱን በነፃነት የመግለፅ መብቱ መጠበቅ አለበት ብለን እናምናለን ብለዋል፡፡

በግብፅ እየተጣሰ ስላለው ሰብአዊ መብት እንደ ምሳሌ ሆሳም ባጋትን ያነሱ ሲሆን፤ አሜሪካ በግብፅ እየባሰ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት እጅጉን አሳስቧታል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሆሳም ባጋት የግብፅ የግለሰቦች መብት ኢንሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ሲሆን የግብፅን የምርጫ ኮሚሽን በትዊተር ገፁ ሰድበሃል ተብሎ ለፍርድ ቀርቧል፡፡

ቢቢሲ

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *