የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከፍተኛ መስዋትነትን እየከፈሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በጤና ሚንስቴር ተመስግነዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሀገር በከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ በነበረችበት በዚህ ወቅት የሚደርሰዉን ተጽዕኖ ለመቀነስ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በተለይም የጤና ባለሙያዎችና የጤና እንክብካቤ ሰራተኞች ቫይረሱን ለመቋቋምና ዜጎችን ከከፋ ስቃይና ከህልፈተ-ህይወት ለመታደግ ሙያቸውንና ህይወታቸውን ጭምር አሳለፈው በመስጠት ከቫይረሱ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው አገልግለዋል፤ እያገለገሉም ይገኛሉ ነዉ ያሉት፡፡

ሚንስቴሩ በቀጣይ ትኩረት ከሚያደርግበት ስትራቴጂዎች አንዱና ዋነኛው ዘመኑ የሚፈልገው የሰው ሀይል እውቀትና ክህሎትን ማጠናከር በመሆኑ፣ የጤና ባለሙያዎቻችን ተነሳሽነትና ባለቤትነት የምንፈጥርበት ከነደፍናቸው የማትጊያ ስትራቴጂዎች መካከል ሰራተኞቻችንን እውቅና መስጠት ነው ብለዋል ሚንስትሯ፡፡

ይህ ሀገር አቀፍ የምስጋናና የእውቅና ሳምንት ከሀምሌ 11-17/2013 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን በዓለም የጤና ድርጅት የጤና ባለሙያዎችና የጤና ሰራተኞች እንዲሆን በተወሰነበት ወቅት የሚከበር ነው ተብሏል፡፡

የምስጋናና እውቅና ሳምንቱ በብሄራዊ ደረጃ በአዲስ አበባ ተጀምሮ በየክልሉ የሚከበር ይሆናል ነዉ የተባለዉ፡፡

ሳምንቱ የጤናና የጤና እንክብካቤ ሰራተኞች ደህንነታቸው ይጠበቅና ተባብረን እንዲሳካ ማድረግ እንችላለን የሚሉ መልዕክቶችን የያዘ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በጅብሪል ሙሃመድ
ሐምሌ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *