51ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በጸጥታ ጉዳዮች ዙርያ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

51ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በሞጆ የተጀመረ ሲሆን በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያቶች በተፈጠሩትን የጸጥታ ችግሮች ዙርያ ምክክር እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡

በጉባኤው ካርዲናል ብርሀነ የሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የካቶሊክ ጳጳሳት በሙሉ በጉባኤው ላይ ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

በዚህ ጉባኤ በሀገራችን ያሉ ወቅታዊ ፖለቲካዊ እና የጸጥታ ሁኔታዎች፣ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ምክንያቶች እንዲሁም በተፈጠሩ ግጭቶች፣ ጦርነቶች ምክንያት የደረሰውን የሰው ልጆች ሞት፣ ስደት ከቤት ንብረት መፈናቀል እና የንብረት ውድመት አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረገ ተገልጿል፡፡

እንደዚሁም አስፈላጊ በሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታዎች ላይም ጉባኤው አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሏል፡፡

በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል አሁንም ድረስ የሚስተዋሉትን አሳሳቢ ሁኔታዎች በተመለከተ ልዩ ጸሎት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው፡፡

እስካሁን ድረስም በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ቤተክርስቲያኗ ያከናወነቻቸውን ተግባራት በጉባኤው ላይ ይቀርባሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡

ጉባኤው ወደፊትም ሊደረጉ በሚገባቸው አስቸኳይ ድጋፎችን በተመለከተ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሏል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች የማሕበራዊ ልማት ዘርፎች የምታከናውናቸውን አገልግሎቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመመርመር የመፍትሄ አቅጣቻዎችን ጉባኤው ያስቀምጣል ተብሏል፡፡

ጉባኤው ሀምሌ 9 ቀን የሚጠናቀቅ ሲሆን በእለቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በመደገፍ የካቶሊክ ጳጳሳት በየዓመቱ በተለያዩ ስፍራዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ ዘንድሮም ችግኞችን በመትከል ጉባኤው ይጠናቀቃል ተብሏል::

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *