ኤጀንሲው ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ለስኳር ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን ማሰራጨቱን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2013 በጀት ዓመት ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ለስኳር ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን ማሰራጨቱን የስርጭት ቡድን መሪው አቶ ተስፋሁን አብሬ ገለጹ፡፡

የተሰራጩት መድኃኒቶች ለአይነት 1 እና 2 (Type 1 and 2) የስኳር ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን 1 ሚሊየን 887 ሺህ 425 እሽግ ለጤና ተቋማት መሰራጨቱን አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡

ስርጭቱም በአዳማ፣በአርባ ምንጭ፣ በአሶሳ፣ በባህርዳር፣ በደሴ፣ በጋምቤላ፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በሀዋሳ፣ በጅጅጋ፣ በመቀሌ፣ በነገሌ ቦረና፣ በነቀምት፣ በሰመራ፣ በሽሬ፣ በአዲስ አበባ ቁጥር 1 እና 2 ቅርንጫፎች አማካኝነት የተሰራጨ ሲሆን 19 ሚሊየን 880 ሺህ 338 .68 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ቡድን መሪው አስረድተዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *