2ኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት መድኃኒት ፣መሰራጨቱ ተገለጸ ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ 2ኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት መድኃኒት ከሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ማሠራጨቱን የመጋዘን አያያዝና ክምችት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ ማስተዋል አበባው አስታወቁ፡፡

ስርጭቱም በሰመራ፣ በጎንደር፣ በሀዋሳ፣ በባህርዳር፣ በአዳማ፣ በጋምቤላ፣ በደሴ፣ በአሶሳ፣ በጅማ፣ በነቀምት ፣ በጅጅጋ፣ በነገሌ ቦረና፣ በድሬዳዋ፣ በአርባ ምንጭ፣ በአዲስ አበባ ቁጥር 1 እና 2 ቅርንጫፎች አማካኝነት ለ1008 ወረዳዎች ተደራሽ እንደሚሆኑ ባለሙያዋ አስረድተዋል፡፡

የተሰራጩት የክትባት መድኃኒቶች 325 ሺህ 887 ዶዝ መጠን እንዳላቸው ወ/ሮ ማስተዋል የገለጹ ሲሆን 583 ሚሊየን 611 ሺህ 475 ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል ሲሉ ተናግዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *