ሳውዲ አረቢያ 60 ሺህ የሚጠጉ የሐጅ ተጓዦችን ብቻ ተቀብላ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡

በየአመቱ ከመላው አለም በርካታ ቁጥር ያለው የእስልምና እምነት ተከታዮች የሐጅ ጉዞ የሚያደርጉባት ሣውዲአረቢያ በዘንድሮ ዓመት 60 ሺህ የሚጠጉ የሐጅ ተጓዦችን ብቻ ተቀብላ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡

ከመላው አለም ወደ እዚህ ስፍራ እስከ 2.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የሐጅ ጉዞ ያደርጉ የነበረ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዘንድሮ 60 ሺህ ሰዎች ብቻ ናቸው ወደ ስፍራው ያቀኑት፡፡

የሐጅ ጉዞ እንዲያደርጉ የተፈቀደላቸውም የሳውዲ አረቢያ ዜግነት ያላቸውን ዜጎች ብቻ ነው፡፡

የሳዑዲ መንግሥት የውጪ አገር ዜጎች ለሐይማኖታዊ ጉብኝት አገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱ ይታወሳል፡፡ እገዳው ወደ መካ እና መዲና የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ጉብኝቶችንም እንደሚያካትት መገለጹ የሚታወስ ነው ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሳዑዲ አረቢያ ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተባቸው አገራት የሚመጡ ሰዎች ወደ ድንበሬ ድርሽ እንዳይሉ ማለቷም አይዘነጋም፡፡

ከአምስቱ የእስልምና መሰረቶች አንዱ የሐጅ ጉዞ ሲሆን ማንኛውም የእስልምና ተከታይ አቅሙ ሲፈቅድ ቢያንስ አንድ ጊዜ በሕይወት ዘመኑ የሐጅ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲሳተፍ ይጠበቃል፡፡

ከሐጅ ቀደም ብሎ በብዛት ይደረግ የነበረው የኡምራ ሥነ ሥርዓት ዘንድሮ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡

ሆኖም ኡምራ በማንኛውም የዓመቱ ወቅት የሚካሄድ ሃይማኖታዊ ሥርዓት እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡

የሳውዲ መንግስት በአሁኑ ወቅት ከመንፈሳዊ ተጓዦች ውጭም ቢሆን መካና መዲና እንዲሁም ዋና ከተማዋ ሪያድ ድንበሮቻቸውን መዝጋቷን አልጀዚራ ዘግቧል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *