የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እስራኤል እንድታደራድራቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓን ማሪቭ የተባለው የእስራኤል ጋዜጣ ዘግቧል ፡፡
ጃኪ ሁጊ የተባለው የእስራኤል አምደኛ እንደተጻፈው ግብፅ ውስጥ እስራኤል በግድቡ ጉዳይ ካይሮ እና አዲስ አበባን በድብቅ እያደራደረች ነው፤ የሚል መረጃ ቢኖርም እውነቱ ግን ተቃዋሚ ቡድኖች አል-ሲሲ ከእስራኤል ጋር እንደሚተባበሩ ለማሳየት የተጠቀሙበት ዘዴ ነው ብለዋል፡፡
በጃኪ ሁጊ መረጃ መሠረት ግብፅ የእስራኤልን መንግስት ከሁለት ዓመት በፊት እንድታደራድር የጠየቀች ቢሆንም ቴል አቪቭ ግን ሀሳቡን አልተቀበለችም ነው ያሉት፡፡
የእስራኤል ዲፕሎማሲ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የሌሎችን ችግር የመፍታት ፍላጎት አልነበረውም ፣ ይህ የችሎታ ጥያቄ አይደለም ፣ ይልቁንም የፖለቲካ ባህል ነው ፣ ምክንያቱም እስራኤል እራሷን እንደ ቀጠናው ሀያል አድርጋ አትመለከትም ፡፡
ራሷን እንደ ሀያል አገር ብትቆጥር እንኳን በዲፕሎማሲ ሳይሆን በወታደራዊ ሀይል ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ12 ቀን 2013 ዓ.ም











