የባይደን አስተዳደር ለመጀመርያ ጊዜ ከጓንታናሞ እስረኛ ፈታ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የጆ ባይደን አስተዳደር ከጓንታናሞ አንድ እስረኛ መፍታቱት አስታወቀ፡፡

ከፈረንጆቹ 2002 አንስቶ በጓንታናሞ እስር ቤት የነበረው የሞሮኮ ዜግነት ያለው አብድል ላቲፍ ናስር የተባለው ግለሰብ ከእስር እንዲለቀቅ የባይደን አስተዳደር የወሰነው፡፡

ፍርድ ሳይሰጠው እስካሁን ድረስ በእስር የሰነበተው ግለሰቡ በ50 ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ለእስር የተዳረገው የአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ተግባር ላይ ተሳትፎ ነበረው በሚል ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ግለሰቡ ከውጭ ሀገራት ጋር በማበር ህገ-ወጥ ሰነድ በማዘጋጀት ክስ ተመስርቶበት እንደነበረም ነው የተገለጸው፡፡

በ2016 የአሜሪካ ፍርድ ቤት ግለሰቡ ላይ ምንም አይነት የወንጀል ክስ አላገኝሁም በሚል ከእስር እንዲፈታ ወስኖ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ተፈጻሚ መሆን አልቻለም ነበር፡፡

ከዚህ ቀደም አሜሪካንን ያስተዳደሩ ፕሬዝዳንቶች ጓንታናሞ እስር ቤት እንዲዘጋ ትልቅ ስራ የሰሩ ቢሆንም አልተሳካላቸውም፡፡

ጓንታናሞ የሚገኙ እስረኞች በሀገሪቱ ህግ መሰረት እጅግ ከባድ ወንጀል የፈጸሙ በመሆናቸው እስር ቤቱ መዘጋት የለበትም የሚሉ ክሶችም ሲቀርቡ ነበር የሰነበቱት፡፡

አብዛኛዎቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ከዚህ በፊት እስረኛን ሲፈቱ አይስተዋልም ነበር አሁን ጆ ባይደን ይህንን ታሪክ የቀየሩ ነው የሚመስለው፡፡

ላለፉትን ዘጠኝ አመታት ያለ ፍርድ እስር ቤት የማቀቀው ሞሮኮዊውን አብድል ላቲፍ ናስር በአረፋ ዋዜማ ከቤተሰቦችህ ተቀላቀል ተብሎ ከእስር ተለቋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *