የአልሳም ድርጅት ባለቤት ለመቄዶኒያ አረጋውያን ማእከል 12 ሰንጋ በሬዎች ድጋፍ አደረጉ፡፡

የአልሳም ድርጅት ባለቤት የሆኑት አቶ ሀጂ ሳፒር አገነው ለመቄዶኒያ አረጋዊያን ማእከል የኢድ አል አድሀ አረፋ በአልን ምክንያት በማድረግ 12 በሬዎችን ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡

አቶ ሀጂ ሳፒር ከበሬዎች በተጨሪም ለበአል የሚያስፈልጉ ወጪዎችን እና ግብአቶችን በሙሉ ለማእከሉ መሸፈናቸው ነው የተገለጸው፡፡

የመቄዶኒያ አረጋዊያን ማእከል የኤስ ኤም ኤስ ባለሙያ ኢንጂነር ገረመው ሙሉጌታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በነገው እለት የሚከበረው የኢድ አል አድሀ አረፋ በአል አረጋዊየኑ በደስታ እንዲያሳልፉ ለማድረግ አቶ ሀጂ ሳፒር የሰንጋ ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል፡፡

አቶ ሀጂ ሳፒር በተለያዩ ጊዜያቶች ለማእከሉ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበረ የተናገሩት ኢንጂነር ገረመው አሁን በአሉን ምክንያት በማድረግ የበአሉን ወጪ ሸፍነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሁን አቶ ሀጂ ሳፒር የለገሱት በገንዘብ ሲተመን ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ይሆናል ሲሉም ነው አቶ ገረመው የተነገሩት፡፡

የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ ወደ ማእከሉ የሚመጣ ጎብኚ ባለፉት 12 ወራቶች እጅጉን ተቀዛቅዞ የነበረ ሲሆን አሁን መሻሻሎች እየታዩ ነው ተብሏል፡፡

የሰርግ ስነ ስርአቶች፣ የምርቃት፣ የሙት አመት፣ የልደት እና ሌሎችም ክዋኔዎች ለማድረግ ሰዎች ወደ ማእከሉ እየመጡ ነው ተብላል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *