የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ15 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ገለጸ


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2013 በጀት አመት የኢነርጂ ገቢን ለማሳደግ እና ለመሰብሰብ ካቀደው 18 ነጥብ 21 ቢሊየን ብር ውስጥ 15 ነጥብ 45 ቢሊየን መሰብሰብ መቻሉን ገለፀ፡፡

በበጀት አመቱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞች ባልተቋራረጠ መልኩ ማድረስ፣ አዲስ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር ማሳደግ፣ በተቋሙ ደረጃ የተተገበሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የተቋሙን ገቢ በመሰብሰብና በሃገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በግሪድና ከግሪድ ውጭ የሆኑ አዳዲስ ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህም በበጀት አመቱ ለ380 ሺህ 541 ደንበኞች ኤሌክትሪክ ኃይል ማገናኘት መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

የአዲስ የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ በተሰራው ስራ ለ364 የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በዚህም 4320.06 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 3465.30 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እና 946 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ተከላ ተከናውኗል፡፡

የዋናው ግሪድ የማይደርስባቸው ስምንት የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የዘንድሮ በጀት ዓመት የኢነርጂ ሽያጭ ከባለፈው 2012 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር የ4.38 ቢሊየን ብር ወይም የ39.56 በመቶ ጭማሪ ማስመዝገቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጰያውያን
ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *