ሱዳን በህዳሴ ግድቡ ላይ አስገዳጅ ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁንም ጥረቴን አላቆምም አለች

ሱዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ቢጠናቀቅም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌትና አሰራሮች ላይ ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ ጥሪዋን እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ አስታውቀዋል ፡፡

ሃምዶክ የኢድ አል-አድሃ በዓልን አስመልክቶ ለህዝቡ ባስተላለፉት ንግግር የግድቡ ጉዳይ በመንግሥታቸው ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሆኖ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡

የሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ምንም ነገር እናደርጋለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ሱዳን ትሪቡን ዘገባ፡፡

ግድቡ በአለም አቀፍ ህግ አስገዳጅ ስምምነት ሊሞላ ወይም ሊሰራ እንደሚገባው የካርቱም ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሦስቱ አገሮችን የሚጠቅመውን ግድብ ለማሳካት ሱዳን እና ግብፅ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርባለች፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ማክሰኞ ዕለት ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ጋር በነበራቸው ቆይታ በመጋቢት ወር 2019 በሶስቱ ሀገራት በተፈረሙ መርሆዎች መሠረት በክረምት ወቅት

ሁለተኛው ሙሌት መከናወኑን ተናግረዋል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *