ባለፉት 10 ወራት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ህገወጥ ስራ ሲያከናውኑ በነበሩ 6መቶ 50 የደንብ አስከባሪዎች ላይ ከስራ እስከ ማገድ የሚደርስ እርምጃ መውሰዱን ቢሮው ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ባዩ ሽጉጤ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣በከተማዋ በደንብ ማስከበር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ከተሰጣቸው ኃላፊነት ውጭ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል።
ባለፉት 10 ወራት ህገወጥ ስራ ሲሰሩ በነበሩ 6መቶ 50 የደንብ አስከባሪ አባላት ላይ እስከ ስራ ማገድ የሚደርስ እርምጃ ወስደናል ነው ያሉት።
የደንብ አስከባሪዎች በከተመዋ የሚስተዋሉ ህገወጥ ስራዎችን ማጋለጥና መከላከል ሃላፊነት ያለባቸው ቢሆንም ሁሉም የደንብ አስከባሪ ግን ኃላፊነቱን እንደማይወጣ ተነግሯል።
ሁሉም የደንብ አስከባሪ ማለት ባይቻልም በተለያዩ ወረዳዎች ኃላፊነቱን የማይወጣ እንዳለም ነው አቶ ባዩ የገለፁት።
በቀጣይ የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ ቢሮው የቁጥጥርና ክትትል ስራውን አጠናክሮ እንደሚያከናውንም ኃላፊው ነግረውናል።
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ከ 5 ሺህ በላይ የደንብ አስከባሪዎች ያሉ ሲሆን ቁጥሩን ከፍ በማድረግ ህገወጥ እንቅስቃሴን ለመከላከል በትኩረት ይሰራል ነው ያለው ቢሮው።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም











