የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሀዋሳ ኢንዱስተሪያል ፓርክ ለፋብሪካ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ሊያስገነባ ነው

የመኖሪያ ቤት ግንባታውን ለማካሄድ የሚያስችለውን የውል ስምምነት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና የኮርነር ስቶን ሀውሲንግ ደቨሎፕመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲራክ አምባዬ ተፈራርመዋል፡፡

ለሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በ 2.08 ሄክታር ላይ የሚያርፍ ሲሆን ለ6500 የፋብሪካ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ለማቅረብ የሚያችል ሥምምነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመኖሪያ ቤት ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት ላይ ሲውል በውስጡም ከሰራተኞች መኖሪያነት ባሻገር የሰራተኞች መመገቢያ አዳራሾች፣ ሱቆች፣መዝናኛ ቦታዎች፣ባንክ፣ የሰራተኞች ስልጠና መስጫዎች፣ አረንጓዴ ስፍራ፣ክሊኒክ እና ቢሮዎችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የሚገነባው ይህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 13 ሕንጻዎችን ያካተተ ሲሆን የህንፃዎቹ ዲዛይንም የዓለም አቀፍ የሰራተኞችን የመኖሪያ ስታንዳርድ ያሟላ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የህንፃዎቹን ግንባታ ለማጠናቀቅ 18 ወራት ይፈጃል የተባለ ሲሆን ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለውን የቤት አቅርቦት ችግር ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.