ግብፅ እና እንግሊዝ ስለ ፍልስጤም እና ስለ ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በስልክ መነጋገራቸው ተሰምቷል::

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ እና የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስለ ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በፍልስጤም ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ተነግሯል ፡፡

ይፋ በተደረገው መግለጫ መሠረት ሁለቱም መሪዎች የሊቢያ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ጨምሮ በበርካታ የሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በስልክ ተነጋግረዋል፡፡

የግብፁ ፕሬዝደት አል ሲሲ ሀገራቸው በአባይ ወንዝ ውሃ ላይ ያላት ታሪካዊ መብቶች እና የውሃ ዋስትናው አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደሚሹም መናገራቸውን መግለጫውን ጠቅሱ Prensa Latina ዘግቧል፡፡

የግብጹ ፕሬዝደንት በአለም አቀፍ ህግ ተገዢነት እና የአሠራር ህጎች ላይ ፣ ፍትሃዊ እና ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ላይ ለመድረስ ድርድሩን መቀጠል እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፍትሃዊ መፍትሄን ለማምጣትም ድርድሩን እንደገና ለማስጀመር ለሚደረገው ጥረት ጆንሰን ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚደረገዉ የሶስትዮሽ ዉይይትና ድርድር እንዲቀጥል ተደጋጋሚ ጥሪ ስታቀርብ መቆየቷ የሚታወስ ነዉ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *