የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት ለእንቦጭ ማስወገጃ በጀት በአፋጣኝ ካለቀቀ በቀጣዮቹ 2 ወራት አረሙ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚስፋፋ ተነገረ

የጣና ሃይቅና ሌሎች የዉሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ ወቅቱ አረሙ የሚስፋፋበት ወቅት በመሆኑ የፌደራሉ እና የክልሉ መንግስት የበጀት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

በኤጀንሲዉ የብዝሓ ህይወት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ መዝገቡ ዳኘዉ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፤ በተያዘዉ ክረምት አረሙን ለማስወገድ የበጀት ችግር ገጥሞናል ነዉ ያሉት፡፡

አረሙ ከዚህ ወር ጀምሮ እስከ መስከረም ድረስ ባሉት 3 ወራት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚስፋፋ የገለፁት አቶ መዝገቡ፤ በእነዚህ ወራት ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በቅርቡ በተካሄደዉ አገር አቀፍ እንቦጮን የማስወገድ ዘመቻ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነዉን አረም ማስወገድ ቢቻልም አሁንም ክትትል እንደሚያስፈልገዉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ ባለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከበጀት ስጋቱ በተጨማሪ አርሶ አደሮችን ለማሰማራት ችግር እንደፈጠረም ተነስቷል፡፡

ህብረተሰቡ የክልሉና የፌደራሉ መንግስት በዚህ በክረምት ወቅት በሚከናወነዉ እንቦጭን የማስወገድ ስራ ላይ በትኩረት እንዲሳተፍም ጥሪ ቀርቧል፡፡

የእንቦጭ አረም በጣና ሃይቅ ዙሪያ በ30 ቀበሌዎች ከ4 ሺ ሄክታር በላይ የሚሆነዉን የሃይቁን ክፍል ተሸፍኖ የነበረ ሲሆን በዚህ አመት በተሰራዉ ስራ 90 በመቶ ማስወገድ መቻሉን ሰምተናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *