በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የአካል ጉዳት ከመድረሱ ውጪ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች አለመኖራቸው ተነገረ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በኢትዮጵያውያን ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ባለው ሂደት ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን እንደሌሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን በዚህ ወቅት እንዳሉት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ህክምና እያገኙ እንደሆነ ተናግረዋል።

በደቡብ አፍሪካ ካለው የአገሪቱ ኤምባሲ ጋር በመሆን ጉዳዩን እተከታተልን ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ፤ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ያሉ ዜጎች ምን ያህል እንደሆኑ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ነገር ግን በግጭቱ ምክንያት በተፈጠረ ግርግር ፣ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ንብረቶች እንደተዘረፉ መገለፁ ይታወሳል ።

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጃኮብ ዙማ መታሰራቸውን ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው ባስነሱት ግጭች ከ1መቶ17 በላይ ዜጎች መሞታቸው ተነግሯል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

አባቱ መረቀ
ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *