ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ጨዋታ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣ ከአየር ማረፊያ እንዳልወጣ ተሰምቷል፡፡
ማክስኞ ሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ወደ ስፈራው ያመራው ልዑካን ቡድኑ፣ በአውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት የሞዛምፒክና የናይጄሪያ ልዑካን ቡድን ውስጥ የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) የተያዘ መኖሩ በምርመራ በመረጋገጡ ምክንያት፤ ሁሉም ተሳፋሪ በአየር ማረፊያው ውስጥ እንዲቆዩ መደረጉን በስፍራው የሚገኘው የሪፖርተር ስፖርት ክፍል ባልደረባ አረጋግጧል፡፡
ከልዑካን ቡድኑ ጋር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው(ዶ/ር)፤ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ደራርቱ ቱሉ (ኮማንደር)ና የተለያዩ የስፖርት አመራሮች ይገኙበታል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም











