የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ ቡድን ከቶኪዮ አየር ማረፊያ በሠላም ወጥቶ ሆቴል ገብቷል::

ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣ ከአየር ማረፊያ እንዳልወጣ ሲነገር ነበር፡፡

ይህን እንጅ አሁን ላይ መውጣታቸውን የኢትዮ ኤፍ ኤም ባልደረባ ከስፍራዉ አረጋግጧል፡፡

ዑካን ቡድኑ፣ ጃፓን እንደደረሰ የኮቪድ ምርመራ ማድረግ ስለነበረበት እንደተስጓጎለ የገለፀዉ የኢትዮ ኤፍ ኤም ባልደረባ ግርማቸዉ እንየዉ፤ በሰለም ወደ ሆቴል ገብተናል ብሏል፡፡

አብዛኛዉን የአፍሪካ አገራት የኦሎምፒክ ልዑካንን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳጓጓዘ የገለፀልን ጋዜጠኛ ግርማቸዉ እንየዉ፣ በዚህም አንድ ናይጄሪያዊ ግለሰብ በኮቪድ ስለመያዙ በመረጋገጡ ጥብቅ ፍተሻና ምርመራ በመደረጉ ነዉ መጉላላቱ የተከሰተዉ ነዉ ያለዉ፡፡

የኢትዮጵያ ልዑክ ትናንት በጃፓን ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2፡30 ቶክዮ እንደደረሰ የገለፀልን ባልደረባችን፣ በርካታ እንግዶች ስለነበሩ በፍተሻ ምክንያት እስከ ሌሊቱ 11 ሰዓት ድረስ እንደተጉላላ ታዉቋል፡፡

ከዚህ ባለፈ አንድ ኢትዮጵያዊ የኮቪድ ምልክት ታይቶበታል በሚል ተጠርጥሮ የነበረ ቢሆንም ድጋሜ ሲመረመር ግን ከቫይረሱ ነጻ በመሆኑ ልዕኩን ተቀላቅሏል ተብሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በመልካም ሁኔታ ሆቴል ይዞ እንደሚገኝም ሰምተናል፡፡

ከልዑካን ቡድኑ ጋር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እንደሚገኙ ታወቋል፡፡

በአባቱ መረቀ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *