ግብፅ ፕሬዝደንት አል ሲሲ ከስልጣን እንዲነሱ ጥሪ ያቀረበውን ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር አውላለች:: 

የቀድሞው የአል-አህራም ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ግብጽ በኢትዮጵያ ከባድ ሽንፈት እንድትከናነብ ተጠያቂው ፕሬዝደንቱ በመሆናቸው ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው እንዲለቁ የሚጠይቅ ጽሁፍ በፌስቡክ አስፍሮ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ከ 2012 እስከ 2014 ድረስ የአል-አህራም ዋና አዘጋጅ የሆነው አብዱል ናስር ሳላማ ባለፈው ሳምንት ነበር “ያድርጉት ፕሬዝዳንት” “Do it, President” በሚል ርዕስ በፌስቡክ ፁሁፋን ያሰፈረው ፡፡

በውስጡም ሲሲ “ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ በደረሰባት ከባድ ሽንፈት እና ግብፅ በአባይ ውሃ ላይ ያላትን ታሪካዊ መብት ማጣቷን በግል ሃላፊነቱን ለመውሰድ የሞራል እና የስነምግባር ድፍረት ሊኖረው ይገባል” ብለዋል ሲል አረብ ኒውስ ዘግቧል ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን እንዲለቁ እና እራሳቸውን ለግብፅ የፍትህ አካላት እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ጋዜጠኛው ሰላማ በአሌክሳንድሪያ ተይዞ “የሐሰት ዜና በማሰራጨት” እና “ከህግ ተቃራኒ ከተመሰረተ ቡድን ጋር በመስራት” ክስ እንደተመሰረተበት ተነግሯል ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *