ባንኩ ከሀረሪ ክልል የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት “ደራሽ” የተቀናጀ የአገልግሎት ክፍያ ስርአት ለማዘመን ስምምነት አደረገ፡፡
ባንኩ ባደረገው ስምምነት መሰረት የተቀናጀ የክፍያ ስርአቱ በሀረሪ ክልል የሚገኙ የውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያቸውን አንበሳ ሄሎካሽ በተሰኝ የሞባይል ወኪል ባንክ አገልግሎት በኩል መፈጸም ይችላሉ ተብሏል፡፡
ደንበኞች እንደ ከዚህ ቀደም በአካል ቀርበው መክፍል ሳይጠበቅባቸው በመኖርያ ወይም በስራ ቦታቸው ሆነው በእጅ ስልካቸው አማካኝነት የአገልግሎት ክፍያቸውን መፈጸም ያስችላል፡፡
የክፍያ ስርአቱ በሀረር ከተማ የሚገኙ 22ሺህ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከዚህ በፊት ያጋጥማቸው የነበረውን ውጣ ውረድ ሙሉ በሙሉ የሚያስቀይር ከመሆኑም በላይ ጊዜ ቆጣቢ ነው ተብሏል፡፡
ደንበኞች በሞባይላቸው ከሚያደርጉት ክፍያ በተጨማሪም በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአንበሳ ባንክ ቅርንጫፎች እንዲሁም የባንኩ ወኪሎች ጋር በመሄድ የውሀ አገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚችሉበት አሰራር ስርአት የዘረጋ መሆኑም ታውቋል፡፡
አንበሳ ሄሎካሽ ከ600ሺህ በላይ ደንበኞች እንዲሁም በመላ ሀገሪቱ ባሉት ከ3ሺህ በላይ ወኪሎች አማካኝነት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም











